• Home
  • About us
  • Albums
  • Blog

mezmur

  • Home
  • About us
  • Albums
  • Blog

የመጋቢ ታማኝነት መለኪያዎች  

By Abiy Wakuma 

መጋቢነት  ለሰዎች ነፍስ የመትጋት የተከበረ ጥሪ ነው፡፡ ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ወደ ዕብራውያን 13፡7

መጋቢነት በእግዚአብሄር የሚሰጥ ፀጋ እንጂ በሰው አነሳሽነትና ፍላጎት የሚደረግ አገልግሎት አይደለም፡፡ ማንም ሰው ማንንም ስው ለመጋቢነት ሊጠራ አይችልም፡፡ ሰውም ራሱን ለመጋቢነት ሊያሰማራ አይችልም፡፡ የመጋቢነትን ፀጋ ሰጥቶ ሰውን ለመጋቢነት የአገልግሎት ስራ ሊጠራ የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡11

ሰው በአካባቢው ያለውን ክፍተት አይቶ መጋቢ መሆን አይችልም፡፡ ሰው ስለፈለገና ስለተመኘ ብቻ…

Read more

08/10/2023

እግዚአብሔር የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን  

By Abiy Wakuma 

የገቢ ምንጫችሁ የሆነ ሰው ወደዳችሁም ጠላችሁም የወደፊት እድላችሁን ይወስናል፡፡ የገቢ ምንጫችሁን የሚያመጣ ሰው የሚለውን ላለመስማት ከባድ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ነው፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም  የገቢ ምንጫችሁን የሚያመጣ ሰውን ራእይ በህይወታችሁ ታስፈፅማላችሁ፡፡

በገንዘብ ስለተገዙት ባሮች መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ይህንኑ ነው፡፡ ስለባሮች መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እናንተ ክርስትያን ስለሆናችሁ የምታገለግሉትና የምትታዘዙት ጌታን ክርስቶስን ነው እንዲሁም የርስትን ብድራት የምትቀበሉት ከእርሱ ነው እያለ እግዚአብሄር ምንጫቸው መሆን እንዳለበት ያስተምራል፡፡ እግዚአብሄር ቀጣሪያቸውና ከፋያቸው ሲሆን በነፃነት ሰውን በማገልገል እግዚአብሄርን እንደሚያገለግሉ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ…

Read more

08/10/2023

የእብዷ ተዋናይ ታሪክ  

By Abiy Wakuma 

ግብዝነት ራስን አለመሆን ነው፡፡ ግብዝነት ያልሆኑትን መምሰል ነው፡፡ ግብዝነት ሌላውን ሰው ለመምሰል መሞከር ነው፡፡ ግብዝነት ራስን ያለመሆን አደገኛ እና አክሳሪ አካሄድ ነው፡፡

የሆኑትን መሆን እንጂ ማስመሰል ከባድ ነው፡፡ ተፈጥሮን መሆን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ተፈጥሮን መሆን ይቀላል፡፡ ያልሆኑትምን መሆን ግን ይከብዳል፡፡ የሆኑትን መሆን የመሰለ ነፃነት የለም፡፡

አንድ እብድ ድራማ የምትሰራ ሴት በቴሌቪዠን ቃለመጠይቅ ሲደረግላት ሰምቻለሁ፡፡ ድራማውን ስትሰራ እንደ እብድ ነው የምታስበው እንደ እንድ ነው የምትናገረው አኳኋኗ ሁሉ እንደ እብድ ነው፡፡ ታዲያ እንደእብድ ከምትሰራበትን ድራማ ስትጨርስ ወደ ጤነኝነት ሃሳብ ንግግርና አካሄድ ለመመለስ 2 ሰአት እንደ ሚፈጅባት በቃል መጠይቁ ላይ ስትናገር ሰምቻሉ፡፡

ይህች ሴት እንደ ጤነኛ ለመሆን ምንም ጥረት አይጠይቃትም፡፡ ጤነኛ ስለሆነች…

Read more

08/10/2023

ዘይት መሸጥ ችግሩ ምንድነው ? 

By Abiy Wakuma

ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን ከተባረክናባቸው በረከቶች አንዱ የስጋ ፈውስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ በኩል የሃጢያታችንን እዳ እንደከፈለና ነፍሳችን ከሃጢያት ነፃ እንዳወጣ ሁሉ እንዲሁ ኢየሱስ በመገረፉና ለስጋችን ፈውስና ጤንነት ሙሉ ዋጋ በመክፈሉ ፈውስ የእኛ ነው፡፡

ስለዚህ ነው የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች በታመመ ሰው ላይ ዘይትት ቀብተው እንዲፀልዩለት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች ሃላፊነት በቤተክርስትያናቸው ስለፈውስ ማስተማር ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናስተምር የእግዚአብሄ ህዝብ እግዚአብሄር ለእርሱ ያለውን የፈውስ አላማ ሲረዳ ይፈወሳል፡፡ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ይመጣልና፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 1017

የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች በግልፅ እንደተፃፈው የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝ…

Read more

02/06/2021

እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ 

By Abiy Wakuma 

እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡19

እምነት ታላቅ የክርስትና ሃይል ነው፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፡፡ እምነት እጅግ ታላቅ ሃየለን ይሰጠናል፡፡ እምነት የማያስችለን ነገር የለም፡፡

ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23

ነገር ግን ሃይል ካልመቆጣጠሪያው መንገድ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ካለመቆጣጠሪያ መሳሪያው ብቻውን አደገኛ ነው፡፡ እምነትና በጎ ህሊና ይኑርህ የሚለው ለዚህም ነው፡፡

ምክኒያቱም እምነት እንደ መርከብ ግዙፍና ብዙ ስራዎችን ሊሰራ የሚችል ነገር ነው፡፡ በጎ ህሊና ደግሞ ያንን ታላቅ መርከብ ሊቆጣጠር የሚችልና ወደሚፈለግበት ቦታ ሊያደርስ የሚችል መሪው ነው፡፡

ታላቅ መርከብ መሪ ባይኖረው እጅግ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ያለበጎ…

Read more

02/02/2021

First Prev 1 2 Next Last

  

    Recent Posts     

  እግዚአብሔር የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን

እንደ እንጀራ ይሆኑልናል

የስግደት አደጋው

ለጭንቀት ጥያቄ  የተሳሳቱ መልሶች

ስንሞት ምን እንሆናለን

                

www.mezmur.com

All rights reserved 2023

Some images ©

  • Log out
Powered by Bandzoogle

notes
0:00/???
  1. 1
    የፀሎት ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ 1:20:44
    የፀሎት ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ

    Share link

    0:00/1:20:44
  2. 2
    የፅሞና ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ 1:08:16
    የፅሞና ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ

    Share link

    0:00/1:08:16
  3. 3
    የአምልኮ ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ 1:02:13
    የአምልኮ ጊዜ መዝሙሮች ስብስብ

    Share link

    0:00/1:02:13
0:00/???